ኢናብ ቴክ – ክፍል ስምንት _ ቡክወርም

ክፍል ስምንት _ በቡክወርም መጽሀፍትን ማንበብ፣ ተደራሽ ያልሆኑ የአማርኛ ጽሁፎችን ጨምሮ

በቴክኖሎጂ ዜናዎቻችን፣ ቲክቶክ የተሰኘው የሞባይል ቪዲዮ መመልከቻ አፕሊኬሽን ከነጉግል ስለመብለጡ፣ አፕል ኩባንያ ወደ ገበያ ስላወጣው አዲስ ስልክ፣ የቀድሞው የአሜሪካ ፕረዚደንት ስላስጀመሩት አዲስ የማህበራዊ መገናኛ እና ሌሎችም ቴክኖሎጂ ነክ ወሬዎች እንነግራችኋለን።
በኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍል ቡክወርም ስለተሰኘ የዲጂታል መጽሀፍትን በስክሪን ሪደር አማካይነት ለማንበብ የሚያስችል እና ሂደቱን የሚያቀል ሶፍትዌር የተወሰነ ማብራሪያ እናቀርባለን። በተለይ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች አማርኛ ጽሑፍን ከስካንድ ዶኪውመንትስ ለማንበብ ማስቻሉ ለየት ያደርገዋል።
በፖድካስቱ የተጠቀሰውን ቡክወርምን ከዚህ ያውርዱ።](http://ethionab.org/wp-content/podcast/Bookworm-2022.1a5-x86-setup.exe)

Saturday April 9th, 2022 Podcasts
About

Skip to content