የአይነስውራንን ችግር የሚቀርፍ ቴክኖሎጂን ለመፍጠር ፍላጎቱና ችሎታ ያለው ሰው እንፈልጋለን

በተለይም፦
1ኛ በኣማርኛ፣ በትግሬኛ፣ በግእዘኛ እና በመሳሰሉ ሀገራዊ ቋንቋዎች በሀርድ ኮፒ የተዘጋጁ ሰነዶችን ኦሲኣር ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እስካን የተደረገን ጽሑፍ ወደኤዲተብል ፎርማት መለወጥ የሚያስችል ሶፍትዌር ወይም ፕላትፎርም የሚሰራልን ሰው እንፈልጋለን። ሥራውን በተመለከተ ጋይድ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን።

በ2ኛነት የኢትዮጵያ ገንዘብን መለየት የሚችል የሞባይል መተግበሪያ የሚሰራልን ሰው እንፈልጋለን።

በ3ኛነት የአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግሬኛ እና የመሳሰሉ ሀገራዊ ቋንቋዎች ላይ ድምጽን መረዳት የሚችል (voice recognition) ሶፍትዌር ከማኅበራችን ጋር በመተባበር የሚሰራ ሰው እንፈልጋለን።
ይህ በሶፍትዌር መልክ የሚሰራ የሞባይል ወይም የዴስክቶፕ መተግበሪያ ሊሆን የሚችል ሲሆን ጥቅም ላይ የሚውልበትን መንገድ ማኅበራችን አቅጣጫ የሚሰጥ ይሆናል።

በ4ኛነት ከእንግሊዘኛ ወደአማርኛ እና ከአማርኛ ወደእንግሊዘኛ እንዲሁም በሌሎች ሀገራዊ ቋንቋዎች መዝገበ ቃላት በዴስክ ቶፕ አፕሊኬሽን እና ሞባይል አፕሊኬሽን መልኩ የሚሰራልን ሰው እንፈልጋለን።

በ5ኛነት የአማርኛ፣ የግእዘኛ እና የትግሬኛ ጽሑፍን በጥሩ ድምጽ የሚያነብ እስክሪን ማንበቢያ (screen reader) ሶፍትዌር የሚሰራልን ሰው እንፈልጋለን።

6ኛ የማኅበራችንን አፈጻጸም የሚያሳድጉ እና የሰነድ አያያዝ የሚያዘምኑ ዳታቤዞችን፣ ዌብሳይት ግንባታዎችን፣ የሲስተም ሥራዎችን የሚሠራ ሰው እንፈልጋለን።

ከላይ የተጠቀሱም ባይሆኑ ለአይነስውራን በጣም የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እሰራለሁ የሚል ሰው ከማኅበራችን ጋር አብሮ ቢሰራ ደስተኛ ነን። ማኅበራችን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ፍላጎቶች ግን ይኖራሉ። በስራዎቹ ሁሉ ማኅበራችን ሥራውን በበላይነት የሚቆጣጠር፣ አቅጣጫ የሚሰጥ፣ መረጃዎችን የሚሰጥ፣ ምርቱ የሚያስፈልጉትን መመዘኛዎች የሚያስቀምጥ፣ የምርቱን ውጤታማነት የሚያረጋግጥ መሆኑን እንገልጻለን። ሥራዎቹ በበጎ ፈቃድ ወይም በገንዘብ ድጋፍ የሚሠሩ ሊሆኑ የሚችሉ ሲሆን ዝርዝሩን ከማኅበራችን ጋር መነጋገር የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።

ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ከማኅበራችን ጋር አብሮ መሥራት የሚፈልግ ሰው በኢሜል አድራሻችን “wesenalemu@gmail.com” ወይም ደግሞ “wesen-alemu@ethionab.org) እንዲጽፍልን ጥሪ እናቀርባለን።

በቀላል ቴክኖሎጂዎች የአይነስውራንን ህይወት ቀላል እናድርግ!

Skip to content
https://ethionab.org/