የኢትዮጵያ ዓይነሥውራን ብሔራዊ ማኅበር (ኢ.ዓ.ብ.ማ) በዛሬው እለት (ግንቦት 27, 2015 ዓ.ም) በተደረገው ቃለ-መሀላ 16ኛ የማኅበሩ ቦርድ ለ17ኛ ቦርድ ሥልጣኑን ኣስረከበ፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ሲደረግ የነበረው የኢናብ የቅድመ ምርጫ፣ የምርጫና ድህረ ምርጫ እንቅስቃሴ በዛሬው እለት በተደረገው ቃለ-መሀላ 16ኛ የማኅበሩ ቦርድ ለ17ኛ ቦርድ ሥልጣኑን በማስረከብ ተጠናቋል፡፡
በዛሬው እለት ባለፉት ዓመታት ማኅበሩን በተለያዩ የሥራ መደቦችና የአመራር ስፍራ ሲያገለግሉ የነበሩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የ16ኛ ከአዲስ አበባ ምርጫ ጣቢያ ና ከሰበታ ምርጫ ጣቢያ የቦርድ አባላት የነበሩትና የማኅበሩ ፕሬዚደንት የነበሩት አቶ ወሰን ለአዲሱ የቦርድ አባላት ልምዳቸውን ካካፈሉና የነበረውን የማኅበሩን ጠቅላላ እንቅስቃሴ ካብራሩ በኋላ አዲሱ የቦርድ አባላት ማኅበሩን በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ቃለመሀላ በመፈጸም የማኅበሩ የወቅቱ ፕሬዚደንት የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚደንት ከነበሩት አቶ አየለ ቦጋለ እጅ የሥልጣን መረካከቢያ ሰነድ በመፈራረም በይፋ ነባሩ ቦርድ ለአዲሱ ቦርድ ሥልጣኑን አስረክቧል፡፡
በዚህም አጋጣሚ አባላት ያልተቋረጠ ድጋፋችሁን ለአዲሱ ቦርድ በምትችሉት መልኩ በማበርከት ማኅበራችንን በጋራ እንድናሳድገው ጥሪ የቀረበላችሁ መሆኑን በመገንዘብ ተገቢውን አጋርነት እንድታሳዩ መልእክት ቀርቦላቸዋል፡፡

Left to right, Ato Ayele, Ato Ghebrie, Ato Abera, and Ato Sebeibie
The swearing in ceremony of the 17th round Members of the exceutive board
New elected board members with former members
Skip to content
https://ethionab.org/