ኢናብ ቴክ ክፍል 44 – በአውዳሲቲ የማጀቢያ ሙዚቃን ማስተካከል
download the episodeበዚህ ክፍል፣
በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ቲክቶክ የአሜሪካዋን ሞንታና ግዛት ስለመክሰሱ፣ ኒቫ የተባለው የኢንተርኔት መፈለጊያ አገልግሎቱን ማቋረጡን ስለማስታወቁ እና ሞዚላ ፋየርፎክስ ዊንዶውስ 7 እና 8ን እስከወዲያኛው ስለመሰናበቱ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን።
በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ በአውዳሲቲ ማሳያ የመጨረሻው ክፍል ከስር የሚሰማ ሙዚቃን በአውዳሲቲ ከፍ እና ዝቅ እንዲልልን እንዴት እንደምናደርግ በተግባር እንሞክራለን።
በመሰረታዊ ክፍል፣ የጃውስ ልዩ ልዩ ከርሰሮችን እንዴት እንደምናበራ የምንዳስስ ይሆናል።
በአድማጮች አስተያየትም በማይክሮሶፍት ወርድ ጽሁፍ ከጻፍኩ በኋላ ፎንቱ ልክ አይደለም እየተባልኩ ነው፣ ቶክባክ እንደጂሺዎ አልፈጥን አለኝ፣ ኤንቪዲኤ አኖውን፣ አኖውን እያለ ምንም አያነብልኝም፣ ለሚሉ እና ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ አካትቻለሁ።
ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ።
ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ።
ቴሌግራም ላይ @enabtechpod እና @enabtechbot በመግባት ትችታችሁን ለመላክ እና አድማጮቼን እንዳውቅ ሰርቬይ ልትሞሉልኝ ትችላላችሁ።
በዝግጅቱ የተጠቀሱትን አውዳሲቲን ከዚህ፣ አውዳሲቲ ኤንቪዲኤ አድኦንን ከዚህ ያውርዱ።