በኤምፒ3 ዳይሬክት ከት ትራኮችን ከአልበም ማውጣት

በዚህ ክፍል፣ በዜና ጊዜ፣ ዊንዶውስ 11 ክልከላ ላደረገባቸው ኮምፒውተሮች አፕዴት እየለቀቀ ስለመሆኑ፤ ቲክቶክ የተባለው የቪዲዮ መመልከቻ አፕ ታዋቂውን ዩቱብን እየበለጠው ስለመሆኑ እናወራችኋለን።
በኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍል ደግሞ ኤምፒ3 ዳይሬክት ከት የተባለውን ሶፍትዌር በመጠቀም እንዴት አድርገን አንድ ፋይል ከሆነ አልበም ትራኮችን ነጣጥለን እንደምናወጣ በተግባር እናሳያለን።
በመሰረታዊ ክፍል፣ ከአባከስ ቀጥሎ ስለመጡት የኮምፒውተር ቀዳሚዎች እንተርካለን።
በፖድካስቱ ከተጠቀሱት ኤምፒ3 ዳይሬክት ከትን ከዚህ ያውርዱ።
የኤንቪዲኤ ኤምፒ3 ዳይሬክት አድ ኦንን ከዚህ ያውርዱ።

Play
Play
Skip to content