ክፍል አራት፣ በኤምፒ3 ዳይሬክት ከት ከብዙ ትራኮች በአንድ ጊዜ ማስታወቂያዎችን መቁረጥ

በዜና ጊዜ፣ ቢንግ በተሰኘው ሰርች ኢንጅን ጉግል አንደኛ ደረጃ ተፈላጊ ቃል ስለመሆኑ፣ በአውሮፓ ዩኤስቢ ሲ የተባለው ቻርጀር አስገዳጅ ይደረጋል መባሉ፣ በአመቱ መጀመሪያ አፕል ወደ ገበያ ስላወጣቸው አራቱ የአይፎን አይነቶች፣ ማይክሮሶፍት ኦፊስ 2021 የሚባል ቨርዥን ስለመልቀቁ እና ሌሎች ቴክኖሎጂ ነክ ወሬዎችን እናወራችኋለን።
በኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍል ደግሞ ኤምፒ3 ዳይሬክት ከት የተባለውን ሶፍትዌር በመጠቀም ከብዙ ትራኮች በአንድ ጊዜ ማስታወቂያዎችን ቆርጠን እንደምናስወግድ እና ለግላችን ለስልክ ጥሪም ሆነ ለሌላ ምክንያት የምንፈልገው የሙዚቃ ክፍል ቆርጠን እንደምናስቀር በተግባር እናሳያችኋለን።
በመሰረታዊ ክፍል፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ለንግድ ወደ ገበያ ስለገቡት የኮምፒውተር አይነቶች እና ስለኮምፒውተር ትውልዶች እንነግራችኋለን።
በፖድካስቱ ከተጠቀሱት ኤምፒ3 ዳይሬክት ከትን ከዚህ ያውርዱ።
የኤንቪዲኤ ኤምፒ3 ዳይሬክት አድ ኦንን ከዚህ ያውርዱ።

Play
Play
Skip to content